የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ሳምንት 2025 መክፈቻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አፍሪካ የወደፊት የትራንስፖርት ጉዞን በመቅረጽ ረገድ ቀዳሚውን ቦታ እንደምትወስድ ገልጸዋል ።
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም አፍሪካ ሌላ ቦታ የተሰሩ ቴክኖሎጂዎች ተቀባይ ብቻ አትሆንም እንደአህጉር የራሳችንን የትራንስፖርት ዘርፍ ቀጣይ ጉዞ በራሳችን መንገድ እና አቅም እየቀረጽን እንሄዳለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ እንደሀገር አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት ከፖሊሲ ጀምሮ ለኤሌክትሪክ መኪኖች የተደረጉ እስከ ታክስ ማበረታቻዎች ያደረገቻቸውን ድጋፎች ጠቁመዋል።
የአረንጓዴ ትራንስፖርት ትሩፋቶችንም ሲገልጹ የአፍሪካ ምድር ጤናማ ሲሆን፣ ወንዞቻችን ንጹህ ሆነው ሲፈሱ፣ አየራችንም ንጹህ ሲሆን ውጤቱ ከአፍሪካ አልፎ ለመላው ዓለም ይደርሳል ብለዋል።
ሳምንቱ/ጉባኤዉ''Charging Change:-Building Africa's EV Ecosystem From Grid to Garage" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ሲሆን ዋነኛ ዓላማዉ አፍሪካዉያን ታዳሽ ኢነርጂን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በሚያስፋፉበትና
ተደራሽ :አካታችና ከብክለት የፀዳ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አገራችንን ጨምሮ ልምድ የሚለዋወጡበትና የወዳፊቱን አቅጣጫ የሚተልሙበት ነዉ።
በጉባኤው ክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች :የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።