አዲስ የሚገነባው አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የሀገራችን ስትራቴጂክ ፕሮጀክት ነው፡፡
አዲስ የሚገነባው አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የሀገራችን ስትራቴጂክ ፕሮጀክት ነው፡፡” ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ
መጋቢት 12/2017 ዓ.ም (ትሎሚ)፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው አዲሱ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የሀገራችን ስትራቴጂክ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ አምስት እና ስድስት ወራት አብዛኛው የፋይናንስ እና የዲዛይን ስራው ሲጠናቀቅ ግንባታው እንደሚጀመርም ገልጸዋል፡፡
በአፍርካ ትልቁን ኤርፖርት ለመገንባት በርካታ ስራዎች እየተሰሩም ነው ያሉ ሲሆን የኤርፖርቱ ግንባታው በፋይናንስ ደረጃ ሲታይ ከህዳሴው ግድብ በላይ ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል ፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመላው ኢትዮዽያ እና የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮዽያ አየር መንገድ መዳረሻዎችን፤ የአውሮፕላን ብዛት በማሳደግ እና ምልልሱ በመጨመሩ ትርፋማነቱ ጨምሯል ብለዋል፡፡
የአትዮጵያ አየር መንገድ ዳር- አል- ሀንዳሽ (Dar-Al-Handash) የዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት በመቅጠር በቢሾፍቱ የሚገነባውን አዲስ ኤርፖርት ፕሮጀክት እያስጠና ይገኛል፡፡
አማካሪ ድርጅቱ አዲሱን ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከተለየዩ አውራ መንገዶች ከአዲስ አበባ እስከ ቢሾፍቱ የሚገኙ ከተሞች መካከል ትስስር በመፍጠር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ጋር በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር ጥናት እያካሄደ ይገኛል፡፡
አዲስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገንብቶ አገልግሎት ሲጀምር በዓመት እስከ ስልሳ ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ እንደሚችልም ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ስዓት 143 መዳረሻዎች እና 198 አውሮፕላኖች አሉት፡፡