የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር የተጠሪ ተቋማት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻፀም አበራታች መሆኑ ተገመገመ::

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በኩል የኤርፖርት መሠረተ ልማት የመገንባት እና የሀገሪቱን የኤርፖርቶች መዳረሻ የመጨመር፣ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነትን የማስፋፋት፣ የኤር ናቪጌሽን መሠረተ ልማት በመገንባት፣ አቪዬሽን ኢንዱስትሪው እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፆ የማሳደግ፣ የአየር ትራንስፖርት አደጋ ሥጋትን መቀነስ እና ደህንነት የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን ተብራርቷል፡፡

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ጋር ተያይዞ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የወጡ ህጎች ተግባራዊ የማድረግ፣ በመንገድ ደህንነት ላይ የቁጥጥር ስራዎች መሰራታቸውን፣የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ የመንገድ ደህንነት ኢንስፔክሽን ስራዎች፣ አደጋ የሚበዛባቸው ቦታዎች በመለየት ማሻሻያ እንዲደረግባቸው የማድረግ ስራ መሰራቱ ተገምግሟል፡፡

በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን በኩል በዘጠኝ ወራት ውስጥ የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ዕቃዎች የማቀላጠፍ፣ ለአዲስ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ኦፕሬተር ፍቃድ የመስጠት እንዲሁም የሎጂስቲክስ ወጪን መቀነስ ስራዎች መሰራቱን ተገልጿል፡፡

በአትዮ- ጁቡቲ ምድር ባቡር በኩል የሀገሪቱን ገቢና ወጪ ጭነት የማጓጓዝ፤ የመንገደኞት ትራንስፖርት አገልግሎትን የመጨመር፣ የባቡር መሰረተ-ልማት ጥገና በማድረግ ተደራሽነትን የማሻሻል፣ የባቡር ደህንነትና የመድረሻ ሰዓት ማሻሻል ስራ መሰራቱን ተገልጿል፡፡

በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንሰፖርት በኩል የትራንስፖርት ቁጥር የማሳደግ፣ በከተማና በሀገር አቀፍ ደረጃ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠቱ ተገምግሟል፡፡

በመጨረሻም ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ዘርፉ ለሀገሪቱ ትልልቅ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ትልቅ አስተዋዕኦ እንዳበረከተ ገልፀው በሁሉም ተጠሪ ተቋማት አጠቃላይ የዘጠኝ ወራት አፈፃፀሙ የላቀ ነው ያሉ ሲሆን የተሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የቀሩ ስራዎች በቀሪ ወራት እንዲሰሩ ለሁሉም ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Share this Post