የኢትዮጵያውያንን ለዘመናት የቆየ የመደጋገፍ ባህል ያጠናከረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፥ ሚኒስቴሩ እና ተቋማቱ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎታቸው 11 የአቅመ ደካሞች ቤቶችን በአዲስ ከመተካት በተጨማሪ ለክልሉ አንድ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ይገነባሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ለ1 ሺህ 50 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በክረምት ወቅት የሚከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያውያን የመደጋገፍ ባህልን የሚያጠናክር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራዎች በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ሥራም በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ እና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍን ጨምሮ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በተከናወኑበት መርሐ-ግብር የትራስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የሰመራ ከተማ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።

Share this Post