የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እርስ በርስ መደጋገፍንና መቀራረብን እያጎለበተ ነው ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ
በፕሮግራሙ ችግኝ የተተከለ ሲሆን የ11 አቅመ ደካማ ቤተሰብ ቤት እና አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። ለአንድ ሺ ሀምሳ ተማሪዎችም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎች ተከናውነዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር የፌዴራል ተቋማት በየክልሉ የሚያከናውኑት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ሀገራቸውን ይበልጥ ቀርበው እንዲያውቁ እና የርስ በርስ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ እያደረገ መጥቷል ብለዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አወል አርባ ሁንዴ በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና ተጠሪ ተቋማቱ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላን ጨምሮ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳትና ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አወል አርባ ሁንዴ ፣ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ ፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ደንጌ ቦሩ፣ የአፋር ክልል መንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ክብርት አሚና ሴኮ፣የተጠሪ ተቋማት ሀላፊዎች ፣ የሰመራ ሎጊያ ከተማ ከንቲባ እና ሌሎች ተገኝተዋል ።