ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ አፈጻፀም ለማሻሻል ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ኦፕሬተሮች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ላይ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኦፕሬተሮች በዘርፉ የሚያጋጥማቸውን ከነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዞ፣ ከተሽከርካሪ መለዋወጫ ዋጋ መጨመር ፣ ከተሽከርካሪ አስመጭዎች ብቃት ማረጋገጫ እና ሌሎች በሎጂስቲክሱ ላይ ማነቆ ናቸው የተባሉ ችግሮችን ለክቡር ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የሀገራችንን ሎጂስቲክስ አፈጻፀምን ለማሻሻል የጉምሩክ አሰራርን የተቀላጠፈ የማድረግ ፣የባቡር ፍጥነትን የመጨመር እና ተሽከርካሪዎች በማንኛውም ምክንያት በመንገድ ላይ እንዳይቆሙ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ ከነዳጅ ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ችግር በሀገሪቱ የነዳጅ የአቅርቦት ችግር አለመኖሩን ገልፀው የህዝብ እና የጭነት ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ ነዳጅ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና የተሽከርካሪው የቴክኒክ ብቃት የተረጋገጠ እንዲሁም የትራፊክ አደጋ መንስኤ መሆን የማይችሉ መሆን አለባቸው ብለዋል።