ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ የጃፓኑን ቶሺዩኪ ኦኑማ የICAO ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፋ
ክቡር ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከጃንዋሪ 1፣ 2026 ጀምሮ ለሶስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የተመረጡት የጃፓኑ ቶሺዩኪ ኦኑማን በአመራርነት ዘመናቸው ከአፍሪካ አቪዬሽን ጋር በትብብር እንደሚሰሩ እና የአፍሪካን ተሳትፎ እንደሚጨምሩ እና ጥያቄዎች እንደሚመልሱ አምናለሁ ብለዋል።
በኢትዮጵያ በኩልም ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
ቶሺዩኪ ኦኑማን ከ2020 ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ጊዜያት የቆየውን የጣሊያን ሳልቫቶሬ ስካቺታኖን ተክተዋል።
ሚስተር ቶሺዩኪ ኦኑማ በአሁኑ ጊዜ በICAO ምክር ቤት የጃፓን ተወካይ ናቸው። ከ20 ዓመታት በላይ ልምዳቸው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ጥረቶችን ጨምሮ ብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ፖሊሲን ቀርፀዋል።
ሚስተር ኦኑማ የጃፓን ሲቪል አቪዬሽን ቢሮ (JCAB) ከፍተኛ ምክትል ዳይሬክተር እና የዓለም አቀፍ አቪዬሽን ምክትል ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆኑ ከቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ የLL.B ዲግሪ እና ከፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የLL.M. ዲግሪ አላቸው።