ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ማጠቃለያ - *ክፍል 1*
*ኢኮኖሚ ጉዳዮችን በሚመለከት*
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ከያዛቸው ዋነኛ ዓላማዎች መካከል አንደኛው የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራትን ማረጋጋት ነው። ሁለተኛው የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍና ብዝሃ ተዋናይ በማሸጋገር ጥራት ያላው እድገት ማስመዝገብ ሲሆን ሌላኛው የኢትዮጵያን የእዳ ጫና ማቃለል ነው። በዚህ ረገድ በሁሉም መመዘኛ በኢትዮጵያ አመርቂ የኢኮኖሚ ስኬት ተመዝግቧል።
*ወጣቶችን ለነገ ውድድር የማዘጋጀት ስራ*
ወጣቶችን ለነገ ውድድር ከወዲሁ ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ከኢትዮጵያ አምስቱ የእደገት ምሶሶዎች አንደኛው ቴክኖሎጂ እንዲሆን በማደርግ ለትውልድ ሲሰራ ቆይቷል። ኤአይ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው። በኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛ የሆነውን የኤአይ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት እየተሰራ ነው። ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥለው አንድ ዓመት ውስጥ ስራ ይጀምራል። ይህ ዩኒቨርሲቲ አባቶቻችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ገንብተው ስመጥር እንዳደረጉት ሁሉ ለልጆቻችን ለነገ የተሻለ ዘመን ይዞ ይመጣል።
*ነገን መገንባት*
በቴክኖሎጂ ፣ በህጻናት ትምህርት፣ ከተማ ልማት እና አረንጓዴ አሻራ የሰራናቸው ስራዎች የእኛ መንግሥት የትናንትና እዳ ለመቀነስ እና ዛሬን እድገት ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን ልጆቻችን ነገ ቀና ብለው ከስደት ተቆጥበው በሀገራችን ሀብት ማፍራት እንዲችሉ በእውቅት እየተመራ መሆኑን ያሳያል።