የአፍሪካ ኢ- ሞቢሊቲ ሳምንት 2025 በስኬት ተጠናቀቀ

ለፉት ቀናት ከኬኒያ ናይሮቢ ጀምሮ በኤሌክትሪክ መኪና የተደረገዉን የአንድ ሺ ስድስት መቶ ኪሎሜትር ጉዞ ጨምሮ የኢንዱስትሪ ጉብኚት እና በኢሞቢሊቲ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ የጎንዮሽ ዉይይቶችን ባስተናገደዉ ጉባኤ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በኢሞቢሊቲ ዘርፍ የመሪነት ሚናዋን በብቃት በመግለጽ ተሳትፋለች።

በጉባኤዉ ማጠቃለያ ለአገሪቱ የአረንጓዴ ትራንስፖርት የወደፊት ጉዞ ግልፅ እና መሪ ፍኖተ ካርታ የሆነዉ የ2025-2030 የኢትዮጵያ ኢ-ሞቢሊቲ ስትራቴጂ እና የትግበራ እቅድ ማስጀመሪያ መላው ታዳሚዎች በተገኙበት ተካሂዷል ።

Share this Post