የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አዲስ አርማ /ሎጎ/ ይፋ አደረገ
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በአዲሱ አርማ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርዓት ላይ እንደ ተቋም የተሰጠውን ተልዕኮ፣ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት እና አጠቃላይ ዘርፉን ሊወክል የሚችል አርማ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በአዲሱ አደረጃጀት በተሰጠዉ ተልዕኮ መሰረት ዘርፉን የበለጠ ለማዘመን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ በሁለቱም ዘርፎች በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ቢሆንም አገልግሎት ላይ የነበረው አርማ ይህንን በሚገባ መግለፅ ባለመቻሉ አዲስ አርማ ማዘጋጀት አስፈለሰጓል ብለዋል።
አዲሱ አርማ በዘርፉ እየመጡ ያሉ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ለውጦችን ያካተተ ፣ አራቱንም የትራንስፖርት አይነቶችን ማለትም የመንገድ፣ የአየር፣ የባቡር እና የባህር ትራንስፖርትን በሚያመላክት እንዲሁም በሎጂስቲክስ ዘርፋን በሚገልጽ መልኩ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በአዲሱ አርማ ሀገራችን እየገነባች ያለውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ እውን የማድረግ ቁርጠኝነትን በሴክተራችን ትኩረት በመስጠት ልናሳካው በሚገባ ልክ አሳይተናል ብለዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መሐመዶ አብዶን ጨምሮ፣ ከፌዴራል ተቋማት ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው አንግዶች በተገኙበት አዲሱ አርማ ይፋ ሆኗል።