የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ባደረጉት ንግግራቸው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቅ የአስቻይነት ሚናውን በሚገባ ተወጥቷል ብለዋል።
አክለውም የሁሉም ኢትዮጵያ ህዝቦች አሻራ ያረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ዝግጅት ወቅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ሀገር አቀፍ የሴክተር ጉባኤ የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ማድረጋችን ጉባኤውን ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል ።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አሻድሌ ሐሰን ሰሆኑ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ እንደ ሀገር ለተመዘገቡ ስክቶች ሁሉና ለሌሎች ሴክተሮች የአስቻይነት ድርሻው የላቀ መሆኑን በመግለፅ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በጉባኤው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ፣ ክቡራን ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ በህዝብ ተወካዎች ም/ቤት የመሠረተ ልማትና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጂነር መሀመድ አብዶ ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ተወካዮች፣ የከተማ መስተዳድሮች ፣የክልል ትራንስፖርት ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የሚኒስቴር መ/ቤቱ መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።