የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ቡድን አፋር ክልል ሰመራ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ጎበኘ።
አመራሮቹ 2.4 ኪሎሜትር የሚሸፍነው የአፋር ኮሪደር ልማት ሲጎበኙ በፕሮጀክቱ የአፋር ባህላዊ እሴትን መሠረት ያደረጉ ሶስት ሙዚየሞች፣ በአካባቢው መለያ የሆነው ግመል ቅርጽ ዲዛይን የተደረገ መግቢያ፣አምፊቲያትር፣ state of the art የሆኑ ፋውንቴይኖች፣ የክልሉን ባህላዊ እሴቶችን ተንተርሰው እየተሰሩ ያሉ የሞዛይክ አርት ስራዎች እና ሌሎች በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የአፋር ጊሌ ቅርጽ ያለው አደባባይ መካተቱ ተገልጿል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ፒኤችዲ) ሀሳብ መነሻነት የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት 65 በመቶ የደረሰ ሲሆን በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።