''ኢትዮጵያ የጥንካሬዋ ምንጭ ህብረቷ ነው።'' ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ጨምሮ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በድምቀት አክብረዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ እኛ ኢትዮጵያን ስንሰባሰብ እና አንድ ሰንሆን አንጠነክራለን፣ ደምቀን መታየት እንችላለን ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ የተለያየ ቋንቋ፣ የተለያየ ባህል፣ የተለያየ ሀይማኖት መኖሩ ውበታችን ነው ያሉ ሲሆን ውበታችንን አስጠብቀን አንድነታችንን ከአጠናከርን ኢትዮጵያ በሚመጥናት ደረጃ አናደርሳታለን አሁንም አየሆነ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እየተለወጠች ወደ ቀድሞ ክብሯ እየተመለሰች ነው ብለዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር ደንጌ ቦሩ ሁላችንም የተለያየ አመለካከት የመደማመጥ እና የመቻቻል በዓልን እያዳበርን መሄድ መቻል አለብን ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ደኤታ አቶ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው ብዙሃንነታችን አንድነታችን እና ሀብታችን ነው። ብዝሃነታችንን አንደ ሰጋት ማየት የለብንም ብለዋል።
ዴሞክራሲ እና የፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ በሚል እና ብዝሃነትን እና አካታችነትን ያዳበረ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት በሚሉ ርዕሰጉዳዮች በክቡር ሚኒስትር ዴኤታ ባረኦ ሀሰን እና በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተቋማዊ ለውጥ ስራአስፈጻሚ አቶ ደረጀ ሞገስ የውይይት መነሻ ቀርቧል።
በመጨረሻም ክብር ዶ/ር አለሙ ስሜ ብሄራዊ አንድነታችንን፣ አርበኝነታችንን እና እና የሀገር ፍቅራችንን እያጠናከርን መሄድ አለበን ያሉ ሲሆን ሀገር የምትገነባው በሁላችንም በመሆኑ ስራችንን በግልፅነት፣ ከብልሹ አሰራር ወጥተን የተቋም ስም እየገነባን የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል።