የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለሁለት ተቋማት የስራ ፍቃድ እውቅና ሰጠ።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ለሚገኘው ለአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪ የጥገና ማዕላትን እና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ የስራ ፍቃድ የተሰጣቸው ተቋማት በዘርፉ ያለውን ችግር ከመቅረፍ በአሻገር ኢትዮጵያ የአየር ትራንስፖርት ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም መሰረት የሚጥሉ ተቋማት ናቸው ብለዋል።
ክቡር ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳን ወክለው የተናገሩት ብርጋዲየር ጀነራል መሰረት ጌታቸው የአቪዬሽን ማዕከሉ ከወታደራዊ አውሮፕላን በተጨማሪ የሲቪል አውሮፕላኖችን ለመጠገንና ለጄኔራል አቪዬሽን እድገት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።
በሂደቱም በመስፈርቱ መሰረት አምስቱን የምዘና ምዕራፎች ደረጃ በደረጃ በማለፍ የተመሰከረለት የጥገና ማዕከል ሰርተፍኬት በዛሬው ዕለት ማግኝት መቻላቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮሀንስ አበራ በበኩላቸው የግሉ ዘርፍ ለአቪዬሽን እድገት እያበረከተ ላለው አስተዋጽዎ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዘርፉ መስፋፋት ባሻገር በዘርፉ ተሰማርተው የሚገኙ የግል አየር መንገዶች እየገጠማቸውን ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከጎናቸው ለመቆም ቁርጠኛ አቋም አለው ብለዋል።