የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶች፦

በዋናነት ሦስት ግቦችን አንግቦ የተነሳው ይህ ሪፎርም፣ በሁሉም መመዘኛዎች ስኬታማነቱን እያረጋገጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የሪፎርሙ ዋና ዋና ግቦች እና ስኬቶችም፦

የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት፦ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚታዩ አለመረጋጋቶችን በማስተካከል ጤናማ የኢኮኖሚ ሥርዓት መፍጠር።

የኢኮኖሚ ዘርፎችን ማብዛት፦ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅር ከግብርና መርነት ወጥቶ ዘርፈ-ብዙ፣ የብዙ ተዋናዮች ተሳትፎ ያለበት እና ጥራት ያለው ዕድገት እንዲመዘገብ ማድረግ።

የዕዳ ጫናን ማቃለል፦ የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ።

በዚህም ኢትዮጵያ በእነዚህ በሦስቱ ዘርፎች በሁሉም መመዘኛዎች ሊባል በሚችል ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

Share this Post