ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ስምምነት በአባል ሀገራቱ ተፈረመ።

ዛሬ በጅቡቲ በተከናወነው የፊርማ ስነስርዓት ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ በኩል የኢፌዴሪ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ናቸው።

ስምምነቱ የሎጂስቲክስ አቅርቦትን በማቀላጠፍ እና የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማፋፋት አላስፈላጊ የጉሙሩክ ሂደቶችን በማስቀረት የቀጠናው የንግድ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ እና በሀገራቱ መካከል ያለው የትራንስፖርት ፍሰት በተቀላጠፈ ሁኔታ መከናወን እንዲችል ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመልክቷል።

ስምምነቱ በተጨማሪም የወደብ ተደራሽነትን ለመጨመር እና የአገልግሎት ወጪዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ሲሆን ከባቢያዊ ትስስሮሽን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል ።

Share this Post