የኢትዮጵያ 2025 አቪዬሽን ፎረም ተካሄደ ።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ አቪዮሽን መሰራች በመሆኗና የአለም አቀፉን አቪዬሽን ስታንዳርድ ተጠብቆ በመሰራቱ ጠንካራ አቪዬሽን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በአመት ከ460 በላይ ፓይለቶችን፣ ኢንጂነሮችን እና ቴክኒሺያኖች ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ኩራት የሆኑ ባለሙያዎች እያፈራ ይገኛል ተብለዋል።
በሀገራችን ጠንካራ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ በመፈጠሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን አድርጎታል ተብለዋል ።
የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊ ካስ ኢትዮጵያ ዕምቅ የቱሪዝም ሀብት እንዳላት ገልፀዋል። ይህን የቱሪዝም ሀብት ለዓለም ለማስተዋወቅ የአየር ትራንስፖርት ትልቅ ሚና አለው ተብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው የአየር ትራንስፖርት ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ ሚና ያለው በመሆኑ ጠንካራ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ መገንባት አስፈላጊ ነው ብለዋል።