የ2027 በኢትዮጵያ የሚካሄደውን 102ኛው የአለም አቀፉ የጭነት ትራንስፖርት አስተላላፊዎች ፌዴሬሽን (FIATA)ጉባኤ ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

የትራንፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ የአለም አቀፉ የጭነት አስተላላፊዎች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ስቴፈን ግራበር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የአለም አቀፉ የጭነት አስተላላፊዎች ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ ጉባኤውን እንድታዘጋጅ ስለመረጡ አመስግነው አዲስ አበባ ባለፉት ጊዜያት በርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮችን በስኬት ማዘጋጀቷን እና ይሄንንም መድረክ ባማረ ሁኔታ የምታዘጋጅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአለም አቀፉ የጭነት አስተላላፊዎች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ስቴፈን ግራበር በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ፈጣን እድገት እና ለውጥ እንዲመለከቱ በአለም ዙሪያ ያሉ የማህበሩ አባላት የሚታደሙ መሆኑን በመጠቆም መድረኩ የላቀ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም አመላክተዋል።

በውይይቱ የአለም አቀፉ የጭነት አስተላላፊዎች ፌዴሬሽን (FIATA) የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች እና ሺፕንግ ወኪሎች ማህበር (EFFSAA) ጋር የፕሮግራሙ ዝግጅት ማዕቀፍ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል ።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ ፣ የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች እና ሺፕንግ ወኪሎች ማህበር (EFFSAA ፕሬዝደንት አቶ ዳዊት ውብሸትን ጨምሮ ከሁለቱም ወገኖች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በተገኙበት የአለም አቀፉ የጭነት ትራንስፖርት አስተላላፊዎች ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ጉባኤውን በያዝነው ዓመት ለማካሄድ ማቀዱን አሳውቋል፡፡

Share this Post