“የዘላቂ አቭዬሽን ነዳጅ (SAF) የአዋጭነት ጥናት ውጤት ተግባራዊ ለማድረግ የአገር ውሰጥ እና የዓለም አቀፍ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡” ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ
ዘላቂ የአቭዬሽን ነዳጅ (SAF) የአዋጭነት ጥናት ውጤት ተግባራዊ ለማድረግ የአገር ውሰጥ እና የዓለም አቀፍ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ በሁሉም አካላት ትርጉም ያለው ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን በአፅኖት ተናግረዋል፡፡
የትራንስፖርት ዘርፍ 26 በመቶ የሚሆን የበካይ ጋዝ ልቀት ድርሻ እንዳለው ሚኒስትር ዴኤታው ተናገሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ይሄንን ለመቀልበስ ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች ትገኛለች ብለዋል።
ዘላቂ አቭዬሽን ነዳጅ (SAF) ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪ 80 በመቶ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል የሃይል አማራጭ በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነውም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮሃንስ አበራ በበኩላቸው ዘላቂ የአቭዬሽን ነዳጅ (SAF) ለማልማት የተደረገው የአዋጭነት ጥናት ወቅቱን የጠበቀ ሰለመሆኑ የገለፁ ሲሆን የተካሄደው የባለድረሻ አካላት መድረክ ውጤታማ እንደ ነበር እንሥተዋል።
እንደ ጉሎ ፍሬ፣ጎመን ዘር እና ሰናፍጭ ያሉት የግብርና ምርቶች፤ የእንስሳት ሞራ፣ ከየቤቱ የሚወጣ ደረቅ ቆሻሻ ሁሉ በሚፈለገው ልክ ተብላልቶ አካባቢን ከመበከል ነፃ የሆነ የአውሮፕላን ነዳጅን ለማምረት ያስችላል ተብሏል።
የዛፍ ርጋፊ፣ የምግብ ዘይት ተረፈ ምርት ፣ የሸንኮራ አገዳ ፣ ካሳባ ያሉት ሁሉ ምርቱን ለመስራት አማራጭ እንደሚሆኑ በጥናት መለየቱ የተመላከተ ሲሆን እነዚህ ምርቶች ኢትዮጵያ በብዛት ያሉ በመሆኑ ለአቭዬሽን ነዳጅ በበቂ ደረጃ ማምረት እንደሚቻልም ተነግሯል፡፡
ይህንን ምርት ልክ እንደ ኤታኖል ከመደበኛው የአውሮፕላን ነዳጅ ጋር በመቀላቀል የበካይ ጋዝ ልቀት መጠንን መቀነስ ይቻላል ተብሏል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የትራንስፖርት እና ሎጁስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ በመድረኩ የቀረቡት ዘላቂ አቭዬሽን ነዳጅ (SAF) ለማልማት በተካሄደው የአዋጭነት ጥናት ግኝት እና የቢዚነስ እቅድ አተገባበር በሚመለከት ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች እኔ አስተያየቶች ማብራሪያ እኔ ምላሽ ሰጥተዋል።